400 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ሼክ በክሪ ሳፖሎ ፋውንዴሽን እና ራሀ ሪሊፍ ኤንድ ሁማኒቴሪያል አሶሴሽን ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ በርካታ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ በአራቱም የገጠር ክላስተር አነስተኛ ገቢ ላላቸው 400 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ።

በመርሀ-ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ጨምሮ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ እንዲሁም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት ነው ለተማሪዎቹ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገው ።

ሼክ በክሪ ሳፖሎ ፋውንዴሽን እና ራሀ ሪሊፍ ኤንድ ሁማኒቴሪያል አሶሴሽን ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው የበጎ አድራጎት ስራዎች ሁሉ በዛሬው እለትም ለ 400 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸውን የበጎ አድራጎት ድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሼክ ነስሩዲን ሼክ አብዱረህማን ዳሞታ ተናግረው በቀጣይም መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ስራ አስኪያጁ በእለቱ ያስታወቁት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *