የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ለአስተዳደሩ ሴት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ቀደም ባሉት የመንግስት ስርዓቶች ሴቶች በፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት ሚና ላይ የነበራቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት አጥጋቢ ያልነበረ መሆኑን በመረዳት ብልፅግና ፓርቲ የሴት አመራሮችን ሚና የማሳደግ ስራ በመስራት ላይ መሆኑ ተገለፀ።
ባለፉት ተከታታይ የለውጥ ዓመታት ብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚፈቱና የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በማከናወን በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡን በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው የጠቀሱት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በመሰል ስኬቶች ውስጥ የሴት አመራሮች ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ጨምረው ገልፀዋል።
2018 በጀት ዓመት ከተስፋ ብርሀን ወደ ሚጨበጥ ብርሀን የምንሸጋገርበት መሆኑን በመረዳት ሴት አመራሮች ከወትሮው በተለየ መልኩ በግዜ የለንም መንፈስ ጠንክሮ በመስራት ፓርቲው ያስቀመጠውን ዕቅድ ከስኬት ለማድረስ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አሳስበዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊ ሴት አመራሮች ከመድረኩ በሚያገኙት አቅም በቀጣይ በየዘርፋቸው የክንፏ መዋቅሮች ውስጥ ለሚገኙ አባላት ወርዶ የአቅም ግንባታ ስራዎች መስራት ይጠበቅባቹሀል በማለት የገለፁት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኢፍቱ አህመድ ናቸው፡፡
የስልጠና መድረኩ በዛሬ ውሎው የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ መተዳደሪያ ሕገ-ደንብን በተመለከተ የመወያያ ርዕስ አድርጎ ውሏል።
በቀረበው የመወያያ ፅሁፍ ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩም ተገቢው ምላሽ ተሰጥቶባቸውና በቂ ውይይት ተደርጎባቸው የስልጠናው መድረክ ተጠናቋል።


