ለፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ በተግባር የተደገፈ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ

ይህ የአቅም ግንባታ መድረክ የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ሙያዊ ብቃታቸውን ከማሳደግ ባሻገር በየሙያ መስኩ በየኢንዱስትሪው ተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት ሆኖ መሰናዳቱና የተሻለ ልምድና ተሞክሮዎችን ከአቻዎቻቸው የሚቀስሙበትን ዕድል የሚፈጥር መድረክ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት እንዲሳተፉ እና ስልጠናውን አጠናቀው ሲጨርሱ በማሰልጠን የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና የሥራ ገበያውን ፍላጎት ለመመለስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ ሲሆኑ ገበያው የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት የአሰልጣኞችን ብቃት ተከታታይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም ትኩረት እንደሚሰጠውም በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *