በሃይማኖት መከባበር እና መቻቻል ዙረያ የውይይትና ምክክር መድረክ ተካሄዷል::
በእምነት አባቶች ፀሎትና ምርቃት በተጀመረዉ የዉይይትና ምክክር መድረክ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የድ/ዳ/አስ/ፍ/ፀ/ህ/ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ የአብሮነት እሴቶችን በማሰቀጠል ግጭቶችን በመፀየፍና በማስቀረት ሁል ግዜም ለዘላቂ ሰላም መስፈን ይበልጥ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ለእዚህም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ወሳኝ ስለመሆኑ ነዉ የተናገሩት::
ከቤተሰብ ጀምሮ እሰከ ማህበረሰብ የሰላም ግንባታ ስራዎችን ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አብዱሰለም እንደ ሀገር ከድህነት ወደ ብልፅግና እየተደረገ ባለዉ ሁሉን አቀፍ ሽግግር የሚገጥሙ የፀረ_ሰላም ሀይሎችን እኩይ ተግባራትን ማምከንና በጋራ መከላከል ያስፈልጋል ለእዚህም ሁሉም አካል የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል ነዉ ያሉት::
በዉይይትና ምክክር መድረኩ በሃይማኖት መከባበር እና መቻቻል ዙረያ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ በመድረኩ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ለዘላቂ ሰላም መስፈን የድርሻቸዉን እንደሚወጡም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል::
,በእዚሁ በተቋሙ የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳሪክቶሬት በተዘጋጀዉ የዉይይትና ምክክር መድረክ የሀይማኖት መሪዎች!የአገር ሽማግሌዎች አባ ገደዎች፣ ኡጋዞች፣ የጎሳ መሪዎች የፀጥታና ሌሎች ባለ ድርሻ ተቋማት አመሮችና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል::


