በድሬዳዋ አስተዳደር የተቀናጀ 3ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ

በተቀናጀ 3ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በአስተዳደሩ በገጠር እና በከተማ ከ97 ሺ በላይ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት ይከተባሉ፡፡

በአስተዳደሩ በዛሬው እለት በይፋ የተጀመረው 3ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሀር ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።

በ3ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ላይም የዓለም የጤና ድርጅት(WHO) ተወካይ ዶ/ር ሳራ ማሉሞ፣የUNICEF polio ብድን ፣የሀይማኖት አባቶች፣የጤና ባለሙያዎች የወረዳ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩም ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሀር አስተዳደሩ የፖሊዮ ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ክትባት ዘመቻ ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ስራ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም ዘመቻ መሳካት ወላጆች፣ የሐይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሽማገሌዎች፣ የትምህርቱ ማሕበረሰብ እና ሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ይሱፍ ሰዒድም በበኩላቸው በ3ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ለማከናውን በቢሮ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን አንስተው የክትባት ዘመቻው በተሳካ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት(WHO) ተወካይ ዶ/ር ሳራ ማሉሞ፣የUNICEF polio ብድን መሪ ተ

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ወቅት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *