በአስተዳደሩ ከአጠቃላይ የንፁ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አርባ በመቶ የሚሆነው ለብክነት እንደሚዳረግ ፣ የወጣት አደረጃጀቶች ስነ ምግባር ችግርና ህገ ወጥ የውሃ አጠቃቀምን መከላከል ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።
የመልካ ቁጥር ሁለት የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ ከተደረገ የመስክ ምልከታ በማስቀጠል ሰፊ የመድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን የባለ ስልጣኑ የባለስልጣኑ የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ረመዳን ሙሳ በተጠናቀቀው በጀት አመት ተቋሙ በመደበኛና በፕሮጀክት የተያዙ እቅዶችን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል።
አስተዳደሩ ካለው ውስን በጀት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመልካ ቁጥር ሁለት የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በራስ አቅም እንዲገነባ እያደረገ መሆኑን ፕሮጀክቱ 12 የውሀ ጉድጓዶች፣ 5ሺህ ሜትር ኩብ መያዝ የሚችል ሪዘርቫየር(ቢርካ)፣ ከ58 ኪ. ሜ በላይ የመስመር ዝርጋታ ያካተተ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑ ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ከ40 ኪ.ሜ በላይ የመስመር ዝርጋታው የተጠናቀቀ ሲሆን አስፈላጊ ግብአቶች ግዢ መፈጸሙን ሀላፊው አንስተው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ የአስተዳደሩን የውሃ አቅርቦት በመጨመር ችግር ፈቺ እንደሆነም ተናግረዋል።
በዘርፉ በተለይም ከተደራሽነት ጋር ተያይዞ የውሀ መስመሮች በጨው የመደፈን፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ ህገ ወጥ የውሃ አጠቃቀም፣ የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ መናር እና የበጀት እጥረት በበጀት አመቱ ተግዳሮት የነበሩ መሆናቸውን ኢንጂነር ረመዳን አብራርተዋል።
2018 የመልካን ኘሮጀክት ማጠናቀቅ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና ገቢ አሰባሰብን ማሳደግ በትኩረት እንደሚሰረባቸው ጨምረው ገልፀዋል።
በመድረኩ በተደረገ ውይይት ተቋሙ እየሰራው ያለዉ ስራ አበረታች መሆኑን እና ቀጣይ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነገሮች መኖራቸውን ተናግረዋል ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
ከአፋጣኝ ጥገና፣ የሚቆፈሩ መንገዶችን በአግባቡ ከመመለስ፣ ሰራተኞች ተገቢውን መታወቂያና ባጅ ከመያዝ አንፃር ተቋሙ በትኩረት እንዲሰራባቸው ከተሳታፊዎች ተጠቁሟል።
በውይይቱ ማጠቃለያ የባለስልጣኑ የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ረመዳን ሙሳ የወጣቶች አደረጃጀተወ ህብረተሰቡን በማስተባበር ህገ-ወጥነትንና የስነ ምግባር ግድፈቶችን ለተቋሙ ማጋለጥ እንደሚገባ አጥፊዎች ላይም ህግን የተከተለ አስተማሪ እርምጃ ለመውሰድ ተቋሚ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በአጠቃልይ በአስተዳደሩ በ2018 ዓ.ም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት የውሃ አቅርቦት ብክነትን በመከላከልና ተደራሽነትን በማስፋት የነዋሪውን ጥያቄ ለመፍታት እንደሚሰራ በመድረኩ ተጠቁሟል።


