የድሬዳዋ አስተዳዳር የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ፣ የሴክተር ተቋማት፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወሳል።

በመድረኩ የሴክተር ተቋማት እቅድ አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን በስራ እድል ፈጠራ አፈጻጸም ሁኔታ በተመለከተ በሩብ አመቱ በከተማ ለ3,522 ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ5,376 የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል:: በገጠር ለ962 ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ911 የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ በሪፓርቱ ቀርቦል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ከንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ከህብረት ሥራ ማህበራቶች ጋር በመቀናጀት በሩብ አመቱ 240,000 ሊትር የምግብ ዘይት፣ 1,400 ኩንታል ስኳር፣ 4,500 ኩንታል ጤፍ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ተችሏል።

ከግብርና ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እና በሸማቾች ህብረት አማካኝነት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

የአስተዳደሩ ገቢን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ 10.45 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ በእቅድ የተያዘ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በሩብ ዓመቱ 2.06 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1.76 (85.39%) ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን፡፡

ይህም ከመንግስታዊ ታክስ 1,579,401,892.88 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1,456,806,902.42 ብር (92.24%) ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 479,300,108.23 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 301,160,878.01ብር (62.83%) ተሰብስቧል ።

በአጠቃላይ ከሚሰበሰበው እና ከፌደራል ከሚገኘው ድጎማ በሩብ ዓመቱ አጠቃላይ 2.3 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 2.1 ቢሊየን (92.3%) ወደ አስተዳደሩ ፈሰስ ሆኗል።

የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በተመለከተ በበጀት ዓመቱ 66 አዲስ እና 81 ነባር በድምሩ 147 ፕሮጀክቶች በመተግበር ላይ የሚገኙ ሲሆን እስከ መጀመሪያው ሩብ አመት 8 ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል : : 13 ነባር ደግሞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ:: እንዲሁም 28 አዲስ ፕሮጀክቶች በቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል። 26 አዲስ ፕሮጀክቶች የቅድመ ዝግጅት ስራቸው ተጠናቆ ወደ ትግበራ ምእራፍ በመሸጋገር ላይ ሲገኙ 72 ነባር ፕሮጀክቶች ከ55 እስከ 87% አፈፃፀም ላይ ናቸው።

በኢኮኖሚ ዘርፎች የግብርና ልማት አፈጻጸም የሰብልና ሆርቲካልቸር ልማት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር ፣የወተት ምርት በሊትር፣የእንቁላል ምርት ፣የዶሮ ስጋ በኪ.ግ ፣ የእንሰሳት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር አሁንም ጉድለቶች ስላሉ ሊሰራበት ይገባል የሚል ግምገማ ተደርጎበታል።

በማኑፋክቸሪንግ ልማት የማኑፋክቸሪንግ አምራች ኢንደስትሪዎች የማምረት አቅም ለማሳደግ ፣አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንደስትሪዎች ፣ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ልማትን በተመለከተ እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያሉ ጠንካራ ና ደካማ ጎኖችም ተፈትሸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *