አሽከርካሪዎች ስነምግባረን ተላብሰው በማሽከርከር እንዲሁም ህግና ስርአትን ተከትለው በመንቀሳቀስ ሊደርስ ከሚችል የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ራሳቸውን እና ማህበረሰባሀውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ

የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ከድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ለታክሲ ማህበራት ለባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በተለያዩ ርእሰጉዳዮች ላይ የሚሰጠው ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል። መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት በባስልጣኑ የህዝብ ጭነት ትራንስፖርት ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈለቀ ፈረጃ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በእለቱ መድረክ ሚተላለፉ መልክቶችን በአግባቡ በመውሰድ ወደ መሬት ሊያወርዱ እንደሚገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የእለቱ መድረክም…

Read More