የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ከድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ለታክሲ ማህበራት ለባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በተለያዩ ርእሰጉዳዮች ላይ የሚሰጠው ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።
መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት በባስልጣኑ የህዝብ ጭነት ትራንስፖርት ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈለቀ ፈረጃ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በእለቱ መድረክ ሚተላለፉ መልክቶችን በአግባቡ በመውሰድ ወደ መሬት ሊያወርዱ እንደሚገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የእለቱ መድረክም በአሽከርካሪዎች እና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሀል ያለውን ትስስር በማጠናከር ለአሰራር ቅልጥፍና ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችን የሚወስዱበት እንደሆነ ገልፀው አሽከርካሪውም እንደ ሀገር የወጡ ህግና ደንቦችን በጥልቀት ተገንዝቦ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክር የሚረዳው ነው ብለዋል።
በባለስልጣኑ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ኢንጂነር ሁሴን ጀማል በበኩላቸው ለአሽከርካሪውና ባለንብረቱ በሶስተኛ ወገን መድህን ሽፋን 554/2016 ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን አዲስ እየተተገበረ ባለው የትራፊክ ቅጣት ዙሪያ በተለይ አሽከርካሪው ሲያነሳ ለነበረው ከተገቢ በላይ ተቀጣን ጥያቄም መልስ ሚሰጥ ማብራሪያ ሰተዋል።
በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዋና ኢ/ር ሰዓዳ መሀመድ በበኩላቸው አሽከርካሪዎች ስነምግባረን ተላብሰው በማሽከርከር እንዲሁም ህግና ስርአትን ተከትለው በመንቀሳቀስ ሊደርስ ከሚችል የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ራሳቸውን እና ማህበረሰባሀውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ በወጣው አዋጅ ቁጥር 557/2016 እና በአሽከርካሪ ስነባህሪ ላይ በስፋት ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የአሽከርካሪው ሚና ላይ በስፋት በመድረኩ ገለፃ አድርገዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም መሰል መድረኮች መጠናከር እንዳለባቸው ገልፀው በአንዳንድ የትራንስፖርት እና ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችን ቢታረሙ ሚሉና አዲስ እየተተገበረ ባለው ቅጣት ስርዓትና ችግሮቹን በተመለከተና ሌሎች ሀሳቦች ላይ ጥያቄ አንስተው ከመድረኩ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።


