የፋሲል ግቢ ለዳግም ውልደት በቅቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የፋሲል ግቢ ተውቦ እና አምሮ ለዳግም ውልደት መብቃቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋሲል ግንብ የትም የማናገኘው ውድ ሀብት መሆኑን ጠቅሰው፣ “በእጃችን ስላለ ግን የሚገባውን ዋጋ አልሰጠነውም” ብለዋል። “ይህን አባቶቻችን ያስረከቡንን ወርቅ ሀብት ይዘን ሀገር ብናለማ ኢትዮጵያ ዛሬ ተረጂ እና ለማኝ አትሆንም ነበር” ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል። “ዋናው ችግራችን እኛ እናንስና ታላላቆቹን ጎትተን…


