በድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም አንደኛ ዙር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።
በዚህም በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ኃላፊነት መውሰድና ሀገርን ማገልገል ትልቅ ክብር መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አያይዘውም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ብቃትና ዲሲፒሊን ባላቸው የሰው ሀይል መደራጀቱን ጠቁመው ተቋሙ በቴክኖሎጂ ራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያበለፀገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ምክትል ከንቲባ ሀርቢ በቀጣይ ስልጠናችሁን በብቃት በመከታተል ሀገራችሁን በቅንነት ማገልገል ይገባቹሀል ሲሉ ሽኝት ለተደረገላቸው ወጣቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሀገራችን ሁሌም ጀግኖች ወታደሮችን በየዘመናት ስታፈራ የቆየች መሆኗን በመግለፅ እርስ በእርስ በመዋደድ ለሰንደቅ አላማ በመቆም ህገ-መንግስቱን ማስከበር እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱሰላም አህመድ ናቸው።


