የማህበረሰብ እሴቶችን በመጠቀም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮምሽን በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀት “ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል እና የማህበረሰቡ ስነ-ምግባር ለመገንባት የአደረጃጀት ሚና”በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጠ።

በዚህም በስልጠና በመድረኩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱልጀባር ወጣቶች እና ሴቶች ለሀገር ልማት እና ብልፅግና ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረው፤ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ስነ-ምግባር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

የስልጠና መድረኩ እርስ በእርስ ልምድ መለዋወጫ መድረክ መሆኑንም የገለፁት ኮሚሽነር ፌኑስ የማህበረሰብ እሴቶችን በመጠቀም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑን አመላክተዋል።

የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና በማህበረሰብ ውስጥ ሰፊ ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለባቸው ኮሚሽኑ ተናግረው፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮምሽን በቀጣይ ከወጣት እና ከሴቶች አደረጃጀቶች ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በርብርብ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *