አቶ ይታገሱ ደሳለኝ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ስራን በማላቅ ረገድ ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት በንቃት ስልጠናውን ተከታትለው ለውጤት እንዲያበቁት አሳስበዋል።
ኢንጂነር መሐዲ መሐመድ በበኩላቸው የኤ አይን የላቀ እና የተቀላጠፈ እምቅ አቅም ከተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በማቀናጀት ምርታማነትን እና የአገልግሎት እርካታን ለተገልጋይና ተደራሽ የማድረግ እድል ስለሚፈጥር ከዚሁ አንጻር በትኩረት ስልጠናውን መከታተል ተገቢ ይሆናል ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ የዘርፉ ከፍተኛ ሙሁራን የሚሰጠው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)ስልጠና ዘመኑ የደረሰበትን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትሩፋቶች ከመንግስት ተቋማት አሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በማቀናጀት የተቀላጠፈና የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ያሉት ሙሁራኑ በተለይም ከመረጃ አያያዝና አጠቃቀምና የመረጃ ምዝበራ አደጋ ስጋትንም ከግንዛቤ በማስገባት በሰለጠነ የመስኩ ባለሞያና የበቃ የሰው ኃይል የተደራጁ ተቋማት እንዲኖሩ ለማስቻል የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ሚናው የጎላ መሆኑም ነው በስልጠና ማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የተገለጸው።
ለሚቀጥሉት ተከታታይ ሰባት ቀናት በሚሰጠው በዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የአይ ሲ ቲ( ICT) ባለሞያዎች ወደየተቋሞቻቸው ሲመለሱ በመስኩ ተጨባጭ ለውጥ የሚያስመዘግቡበትን በቂ እውቀትና ክሀሎት
የሚያገኙበት እንደሚሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ኢንጂነር መሐዲ መሐመድ በስልጠና መድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።


