ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብርናን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል። ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። በምርት ደረጃም ሩዝን ወስደን ብናይ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገቢን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

**************** ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው። ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ኢኮኖሚ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል

*************** በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በማዕድን ዘርፍ ትልቅ እመርታዎች ተመዝግበዋል፣ በዚህ ዓመት ያለጥርጥር ዕድገታችን ባለሁለት አሀዝ ይሆናል፣ 900 ቢሊየን ብር የእዳ ሽግሽግ ተደርጎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሞት ድኗል፣ በ2017 ዓ.ም መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ሳይበደር ኢኮኖሚውን መርቷል፣ የኢኮኖሚ ሪፎርማችን ዓለምአቀፎቹ ተቋማት እውቅና የሰጡት እና ለሌሎችም ሀገራት ልምድ የሚሆን ነው፣ በተኪ ምርቶች በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ድኗል፣…

Read More

የዋጋ ንረትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ

************ መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል። ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ ነው። ለነዳጅም 140 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል። በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 ወርዷል። ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል። በቀጣይም ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል።

Read More

“የኢትዮጵያን ዕድገት ጥሩ አፍንጫ ያለው ሰው ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ በሽታ ያውቀዋል። ጥሩ ዐይን ያለው ሰው በማየት ብቻ ሊገነዘበው ይችላል፤ ጥሩ ጆሮ ያለውም ሰው በማድመጥ ሊረዳው ይችላል፤ የኢትዮጵያ ዕድገት የሚያጠራጥር ጉዳይ ስላልሆነ ወይ ዐይናችሁን፣ አፍንጫችሁን ወይም ጆሯችሁን መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቀው።”

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለአዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በተመለከተ ካነሱት

******* አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።

Read More

የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

*********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም በኢትዮጵያ…

Read More

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

***************** የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኖች ከመነሻቸው በቂ ነዳጅ ይዘው ረጅም መንገድ በሚያስጉዛቸው መልኩ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ይህም ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአቬሽን ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ነው ብለዋል፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ሲጀመር ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት ተደርጎበት፣ አርሶ አደሮች ቀድሞ መኖሪያ ቤት ተሠርቶላቸው ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲነሱ መደረጉንም…

Read More

በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

******* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕድንና ጋዝን በተመለከተ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ፤ የማዕድን ሥራችን በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ አንድ ከመቶ ድርሻ እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በተለይም የጋዝ ፕሮጀክት ባስጀመርንበት ሶማሌ ክልል አካባቢ ትልቅ ክምችት መኖሩን አስታውቀው፤ በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ኢትዮጵያ እንዳላት በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅሰዋል። ይህንንም ሃብት ላለፉት ዓመታት…

Read More