*****************
የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኖች ከመነሻቸው በቂ ነዳጅ ይዘው ረጅም መንገድ በሚያስጉዛቸው መልኩ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ይህም ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአቬሽን ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ነው ብለዋል፡፡
የአውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ሲጀመር ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት ተደርጎበት፣ አርሶ አደሮች ቀድሞ መኖሪያ ቤት ተሠርቶላቸው ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲነሱ መደረጉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡
አውሮፕላን ማረፊያው ሲጠናቀቅም በዓመት እስከ 100 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ትልቁ የአፍሪካ አየር መንገድ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀው አውሮፕላን ማረፊያው ተጠናቅቆ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲጀምር፣ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው እንደሚሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለዋል፡፡


