***********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ እጥፋት ነው። ሌሎችም ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ይመጣል ብለዋል።


