ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 05፣ 06፣ 08 እና 09 የብልፅግና ፓርቲ የ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም የብልፅግና ጉዞዋን ለማፋጠን ቀን ከሌት እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ-ግብሩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው የብልፅግና ፓርቲ አባላት “የስንዴ ነዶ” የመደመር፣ የምርታማነትና ከተረጂነት የመላቀቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ጠቁመው፤ባለፉት የለውጥ ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድንና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎች እመርታዊ ለውጦች በማስመዝገብ የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም በሰው ተኮር ተግባራት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው ድሬን ፅዱ፣ ውብና ለነዋሪዎች ምቹ በማድረጉ ረገድም ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት መቻሉን ጠቁመዋል።
በመድረኩ ብልፅግና ፓርቲ ትውልድ የሚያሻግሩ ስራዎችን በመስራት ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ያጋጠሙ ፈተናዎችን ደግሞ ወደ እድል ቀይሮ አበረታች ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉም ተመላክቷል።


