በቢዮ አዋሌ ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎበኙ።

” ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የ 2018 ዓ.ም 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎችን የማስተዋወቅ መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ቢቢዮ አዋሌ ክላስተር ተካሂዷል።

በ 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎችን የማስተዋወቅ መርሀ-ግብር ከተካሄደ በኋላም በቢዮ አዋሌ ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችም ተጎበኝተዋል ።

በጉብኝቱም በገጠር ቀበሌዎቹ በተለይም በመስኖ ውሀ የለሙ እርሻዎችን ጨምሮ የዶሮ እና እንቁላል እርባታዎችን ጎብኝተዋል ። በዚሁ የጉብኝት መርሀ-ግብር ላይም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም የክላስተሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *