በቢዮ አዋሌ ክላስተር ለገቢራና ኢጃ አነኒ ቀበሌ በብልጽግና ፓርቲ ህገደንብና ፕሮግራም ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

    በውይይቱ ስለፓርቲው አስፈላጊነት እንደዚሁም የቀጣይ አቅጣጫ ተብራርቷል፡፡   ተወያዩ በፓርቲም ሆነ በህዝብ ውስጥ ከሁሉም በፊት ሰላምና የህግ የበላይነት መስፈን ይገባል ብለዋል፡፡በቀጣይ ህዝብ ከህዝብ በማቀራረብ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች የሚያደርግ አሰራር ማስወገድ እንደሚገባም ተወያዮቹ በአጽት ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጰያ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆንም መሰራት እንዳለበት በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች አሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ በተደረገው ውይይት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች…

    Read More

      የኢህአዴግ ውህደት ወቅቱን የጠበቀ መሆኑ ተገለፀ

      የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/  የውህደቱ ጥያቄ ለረዥም ጊዜ የቆየ በመሆኑ ውህደቱ አሁን ላይ መደረጉ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን  በውህደቱ ዙሪያ ከድርጅት አባላት ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት ተገልጧል፡፡        በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ገለፃ ያደረጉት በኦ.ዲ.ፒ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የከንቲባው የተፋሰስ ልማት አማካሪ አቶ አብዱጀዋድ መሀመድ የኢህአዲግ የውህደት ጥያቄ ረዥም ጊዜ የቆየ…

      Read More

        የድሬዳዋ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ መርሃ ግብርና ህገ-ደንብ ዙሪያ ተወያዩ

        የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ያገኟቸውን ውጤቶች ለመንጠቅ ሣይሆን ያጡትን ሁሉ ለመመለስ መመስረቱን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከላት አስተባባሪ ዶክተር አለሙ ስሜ ተናገሩ።        ዶክተር አለሙ ስሜ ይህን የተናገሩት የድሬዳዋ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ መርሃ ግብርና ህገ-ደንብ ዙሪያ ሲወያዩ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡      በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ወደ ውህድ ፓርቲ ለመሸጋገር የተጀመረው ከ16 ዓመታት በፊት…

        Read More