በዚሁ እለትም ሰራተኞቹ የችግኝ መንከባከብ ለተቸገሩ ህፃናት የትምህርት መሳርያ ድጋፍ በማድረግና የህፃናት መንከባከቢያን በመጎብኘት እንዲሁም የደም ልገሳ መርሀግብር በማከናወን አሳልፈዋል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ በወቅቱ እንደ ተናገሩት ተቋማት ከሚያከናውኑት የእለት ተእለት ተግባራት በተጓዳኝ በመሰል ማህበረሰብ ተኮር የበጎ አድራጎትና የማህበራዊ አገልግሎት ተግባራት በመሰማራት ለወገን አለኝታነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
እኛም እንደተቋም በእለቱ ያከናወነው ተግባር ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የተቸገሩ ህፃናት በትምህርት ግብአት እጥረት ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ የሚያግዙ የትምህርት ቁሳቁስን በመደገፍ ለወገን ያለንን አለኝታነት ያሳየንበት ነው ብለዋል፡፡
ሌሎች ተቋማትም በመሰል ተግባራት ላይ ሰራተኞቻቸውን በማስተባበር የድርሻቸውን እንዲወጡም አቶ እስቂያስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉን የተረከቡት የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ከሪማ በበኩላቸው የቢሮው ተግባር በተለይ በትምህርት ግብአት እጥረት ትምህረታቸውን ለመከታተል የሚቸገሩ ህፃናትን በመደገፍ ረገድ ጥቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦችም ከዚህ ተግባር በመነሳት መሰል ድጋፍ እንዲያደርጉ በህፃናቱ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በስነስረአቱ ላይ የተሳተፉ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞችም በመል ተግባራት ላይ በመሰማራታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው መሰል ተግባራት በሁሉም ተቋማት እንዲስፋፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


