የበረሃ አንበጣ ዳግም መከሰቱን የአስተዳደሩ ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ::

    ቢሮው በ2012 ዓ/ም ከየመን፣ሶማሊያ እና ጅቡቲ ሀገሮች የገባውን የበረሃ አንበጣ በሶማሌ ክልል አርጎ ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል የደረሱትን የሰብል አይነቶችና የግጦሽ እጽዋት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ሰፋፊ ሥራዎች የተሰሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በአውሮኘላን ኬሚካል ርጭት እና ህብረተሰቡ የተለያዩ ድምጾችን በማሰማት አንበጣው ሰብሉ ላይ እንዳይያርፍ አድርገዋል ብለዋል የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፡፡
    አክሎም አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በአሁን ወቅት የበረሃ አንበጣው በአዲስ መልክ ከዚህ በፊት የጣለውን እንቁላል በመፈልፈሉ ሰብሎቹ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የመከላከል ሥራዎቹ ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡