የድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲ ባለፈዉ አመት በተከሰተዉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሚክኒያት የተቋረጠዉ የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመር የዝግጅት ስራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የገለፁት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ እንደገለፁት በዩኒቨርሲቲዉ በዝግጅት ምዕራፍ የማፅዳት ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸዉን ገልፀዉ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ሆነን ትምህርትና ስልጠና ለማስቀጠል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ባወጣዉ መመሪያው ላይ ሁሉም የዪኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች፣ መምህራንና አመራሮች በቂ ግንዘቤ ይዘዉ በመመሪያዉ መሰረት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማከናወን እንዲችሉ በፕሮቶኮል እና መመሪያዉ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
በመመሪያው በተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ በመምህራንና አመራሩ የተከለከሉ ተግባራትን፣ ግዴታዎችን፣ ሃላፊነቶችንና በምን ደረጃ መማር ማስተማሩ እንደሚካሄድ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ ክፍል ውስጥ፣ መመገቢያ ቦታ፣ ማንበቢያ ቦታ፣ መኝታ ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ላይ ስለሚኖሩ ጥንቃቄዎች ዙሪያ 5 ሺ የሚሆኑ የድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች፣ መምህራንና አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናዉ ላይ ካነጋገርናቸዉ ተሳታፊዎች በሰጡን ሀሰብ እንደገለፀት በዩኒቨርሲቲዉ ጊቢ ውስጥ፣ በተለይም ፣ የመመገቢያ ቦታዎች፣ ማንበቢያ ቦታዎች፣ መኝታ ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ላይ የተለያዩ የማከሚያ ኬሚካሎች መርጨት እና የአጠባ ስራዎችን ሲያከናዉኑ መቆያታቸዉን አብራርተዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን ጋር በጅማ ዩንቨርሲቲ ባካሄደዉ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላለፈ ሲሆን ። በውሳኔውም ለስድስት ወራት ተቋርጦ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ትምህርት ዳግም እንዲጀመር መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡


