የድሬ ዳዋ በ2013 በጀት ዓመት ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትኩረት አስተዳደሩ በመደበኛ ካፒታል የፕሮጀክት (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር ) ፣ ከሌሎች ድጋፎች የተገኘ ( ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር) እና ለቤቶች ልማት (አንድ ቢሊዮን ብር ) በድምሩ (ሶስት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ) የመደበ ሲሆን በዝግጅት ምዕራፍ ወይንም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
የድሬ ዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባዘጋጀዉ በዚህ የፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነባር ፕሮጄክቶች በተለየ ሁኔታ ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ ፣ የማጠናቀቂያ ግዜ እና በፕሮጄክቶቹ ላይ ያሉ ችግሮች ዙሪያ ፕሮጀክቱን የያዙ ተቋማት ፣ የፕሮጄክቱቹ አማካሪዎች እና ፕሮጀክቶቹን እየገነቡ የሚገኙ ኮንትራክተሮች በተገኙበት የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስትና የድርጅት አመራሮች በጋራ የፕሮጀክቶቹን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ፡፡
መድረኩን ምክትል ከንቲባ እና የንግድ፣ኢንደስቲሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር እና ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አልይ የመሩ ሲሆን የአርባ ሰባት ነባር ፕሮጄክቶች አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በፕሮጄክቶቹ ላይ ያሉ ችግሮች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል ፡፡


