የሴቶችና ህጻናት ቢሮ የአስር ዓመት መሪ እቅድና የ2012 ዓ/ም የቢሮው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
በውይይት መደረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንደተናገሩት ሴቶች በኢኮኖሚ በማህበራዊ ፖለቲካዊና መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር እንዲሁም የህጻናት መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚመለከታቸው አከላትን የማስተባበር የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ በሁሉም ሴክተሮች እንዲካተቱ ለማድረግ የሚያስችሉ የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
አክሎም ወ/ሮ ከሪማ አሊ ሴቶች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ንቁ ተሳታፊና ከሚገኘው የኢኮኖሚ ዕድገት እኩል ተጠቃሚ ማድረግ በማህበራዊ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስወገድ እንዲሁም የሴቶች በፖለቲካ መስክ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣የህጻናትን ተሣትፎ ማሳደግና መብትና ደህንነታቸውን ማሰከበር ዙሪያ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ፆታ ጥቃቶችን ለመከላከል በ2012 በጀት ዓመት የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተጠናቀቀበት እና የቀጣዩ የብልፅግና ጉዞ የሚመጥኑ ሀገራዊ የልማት እቅሞችንና ግቦችን እውን ማድረግ ሀገራዊ የአስር ዓመት እቅድ በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር እቅዱን በማዳበር ለቀጣይ ዓመታት በሴቶችና ህጻናትን መብትና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ትኩረት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡


