በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበትን መርሃ-ግብር ተከትሎ በአስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ለመጀመር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ተጠቆመ፡፡

    የአለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከታየ ጊዜ ጀምሮ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መዘጋታቸውን ተከትሎ ከ7 ወራት በኋላ ለማስጀመር በተቀመጠው መርሃ-ግብር በጥቅምት 9 በገጠር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመሩ የተገለጸ ሲሆን በአስተዳደሩ ገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ት/ቤቶች እየተደረጉ ያሉትን ቅድመ ዝግጅቶችን በአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ጉብኝት ተደርገዋል፡፡
    የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዋሂል ክላስተር የሚገኙ የበለዋና የለገ ኦዳ ት/ቤቶችን የመማሪያ ክፍሎች ጽዳትና ሊኖር የሚችለውን የተማሪዎች የክፍል ውስጥ አቀማመጥ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ከት/ቤቶቹ አስተዳደር ጋር ተመካክረዋል፡፡
    ክፍሎቹ ለትምህርት ዝግጁ ማድረጋቸውን የክላስተሩና የት/ቤቶቹ ኃላፊዎች የተናገሩ ሲሆን በተለይም ተማሪዎቹ በአንድ ክፍል እስከ 25 ተማሪ ርቀታቸውን ጠብቀዉ እንዲማሩበት ማዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል፡፡