13ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል “ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሀገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ነው ተከበረው ፡፡

    የበዓሉ አከባበር በአስተዳደሩ ምክር/ቤት ቅጥር ግቢ የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ- ጉባዔ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋና ምክትል አፈ-ጉባዔ አቶ አብዱሰላም አህመድ እንዲሁም የብዙሃን መገናኛና የምክር ቤቱ የስራ ኃላዎችና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
    የሰንደቅ ዓላማው ክብረ በዓል ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመልዕክታቸው እንዳሉት ሰንደቅ አለማችን የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ የአብሮነታችን የዘመናት ከብር ነው ያሉ ሲሆን የዚህ ሰንደቅ አላማችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንዲሁም ሀይማኖቶችን እኩልነት ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡