በሚቀጥሉት 10 አመታት 154,836 ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱ ተገለፀ::

    የቀጣይ 10 አመት የልማት እቅድ ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ በሚገኘዉ የድሬ ደዋ የቀጣይ 10 አመት የልማት እቅድ ላይ የኢኮኖሚ ዘርፍ በቀጣይ 10 አመት ለማከናወን ከታቀዱ ዋና ዋና ግቦች መካከል
    አስተዳደሩ ያለውን የስራ አጥ ምጣኔ አሁን ካለበትየስራ አጥ ምጣኔ 25.3 በመቶ በየዓመቱ በአማካኝ 1.7 በመቶ በመቀነስ በ2022 መጨረሻ የከተማ ስራ አጥ ምጣኔ ወደ 8. በመቶ በማድረስ በአማካኝ በየአመቱ ለ15,483 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል በመፍጠር በድምሩ በ2022 154,836 ዜጎች በሚፈጠረው የስራ እድል የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡ በሥራ ዕድል ይበልጥ ተጎጂ የሆኑትን ወጣቶችን እና ሴቶችን ከሚፈጠረው የስራ እድል ወጣቶች 80 በመቶ ሴቶች 50 በመቶ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን በመድረኩ ላይ ፡፡
    የንግድ ኢንደስቲሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር የኢኮኖሚ ዘርፍ ያለፉት አሥር አመታት አፈፃፀሞችና በቀጣይ አሥር ዓመት የተያዙ የዕቅድ ዋና ዋና ግቦች አቅሪበዉ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
    አቶ አብዲ ሙክታር አክለዉም በኢንቨስትመንት ሴክተር 54,000 የስራ እድል ዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ፣ በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪዎች ለ35,970 ዜጎች የስራ እድል ይፈጠራል ፡፡
    በድሬ ደዋ የቀጣይ 10 አመት የልማት እቅድ ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የድሪጅት አመራሮች የምክክር መድረክ እንደቀጠለ ነዉ፡፡