በአስተዳደሩ የሚኖሩ ነዋሪዎች የኮሮና ቫይረስን በተገቢው መልክ የመከላከል ጥንቃቄዎችን እየተገበሩ አለመሆናቸውን የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በጥናታዊ ፁሁፍ ማረጋገጡን አመልክተዋል፡፡

    ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለአከባቢው ማህበረሰብ የሚሰጠውን አገልግሎቶች አንዱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችን በሚቀረፍበት መንገዶች በጥናት የተደገፉ የመፍትሄ ሀሳቦች ለማቅረብ ጥናቶች ይደረጋሉ፡፡ በዩኒቨርስቲው የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተሰሩትን በተለይም ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ህብረተሰቡ የሚያደርጋቸውን ቅድመ ጥንቃቄ እና ጉድለቶችን የሚያሳይ የተለያዩ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን በህብረተቡ ከሚወሰዱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች ከግማሽ በታች ማለትም (40%) ብቻ የመከላከል ጥንቃቄዎች ይተገብራሉ ብለዋል የጥናቱ አቅራቢና የህክምና ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ በዛብህ አምሳሉ፡፡
    በሌላ በኩል የአስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ራሱን እንዲከላከል የሚሰሩ ሥራዎች በአንድ አንድ ቦታዎች ውስንነቶች መኖራቸውን የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ሰለሞን አክሎም በማህበረሰብ አቀፍ ጥናቶች ዩኒቨርስቲው ትኩረት ሰቶ የተለያዩ የማህበረሰቡ ችግር ናቸው የሚባሉት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች አጥንቶ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚሰጡ ጥናቶች ለማከናወን ሰፋፊ ሥራዎች ማከናወናቸው ገልጸዋል፡፡