ባለፈዉ የፈረንጆች አመት መገባደጃ ላይ የተከሰተዉን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላክል በሀገራችን ወረርሽኙን ለመከላከል ለመቆጣጠር እንዲቻል በኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና በት/ት ሚኒስቴር በወጡ መመሪያዎች ዙሪያ የድሬ ደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የድርጅት አመራሮች ምክክር አካሄዱ፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠርና መከላከልን በወጣዉ መመሪያ ቁጥር 30/2013 በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ሆነን ትምህርትና ስልጠና ለማስቀጠል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ባወጣዉ መመሪያዎች ቀርበዉ በአተገባበሩ እና መመሪየዎቹን ዉጤታማ ለማድረግ በሚቻለበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሄዶበታል፡፡
በምክክሩ ላይ ተማሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት ለመከላከል የተማሪ ወላጆች ፣ ት/ትቤቶች እንዲሁም አመራሮችና መላዉ ህብረተሰብ ተገቢዉን ድጋፍና ርብርብ ማድረግ እንዳለበት በትኩረት ከተነሱ ጉዳዮች ማካከል ዋነኛዉ ነዉ ፡፡


