የኢፌድሬ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ::

    የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን ፤ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤የኢትዮጵያ ብልፅግና ፅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም እንዲሁም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የድሬደዋ ኢንዱስትሪያል ፖርክን መርቀው ከፍተዋል።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መርቀው የከፈቱት የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ነው ተብሏል።
    የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለ1 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል።
    ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል ነው የተባለው።
    የኢንዱስትሪ ፓርኩ 15 ሼዶች ሲኖሩት፤ በአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሠማሩ አራት ኩባንያዎች ሥራ መጀመራቸውም ተገልጿል።
    የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ ነው ::