በድሬዳዋ የተገነባው አዲሱ ቄራ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተመረቀ::

    በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመረቀው ቄራ የስጋ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንዲያስችል ሆኖ የተገነባ ነው።
    ከድሬድዋ ከተማ ወደ ሐረር መውጫ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገነባው ይህ ቄራ በቀን ከ100 በላይ ግመል እና ከ3000 በላይ በግ እና ፍየል በማረድ አቀነባብሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም ያለው ነው ተብሏል።
    በአካባቢው ያለውን ሰፊ የቁም እንስሳት ሀብት በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚያስችል ከመሆኑ ባለፈ ለድሬዳዋና ለአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር ነው።