በጎነት ለወገን በሚል መሪ ቃል የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች መስከረም አስራ ስድስትን በተለያዩ የበጎ ስራ ተግባራት በመሰማራት እለቱን አስበው ውለዋል፡፡

    በዚሁ እለትም ሰራተኞቹ የችግኝ መንከባከብ ለተቸገሩ ህፃናት የትምህርት መሳርያ ድጋፍ በማድረግና የህፃናት መንከባከቢያን በመጎብኘት እንዲሁም የደም ልገሳ መርሀግብር በማከናወን አሳልፈዋል፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ በወቅቱ እንደ ተናገሩት ተቋማት ከሚያከናውኑት የእለት ተእለት ተግባራት በተጓዳኝ በመሰል ማህበረሰብ ተኮር የበጎ አድራጎትና የማህበራዊ አገልግሎት ተግባራት በመሰማራት ለወገን አለኝታነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ እኛም እንደተቋም…

    Read More

      የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከአስተዳደሩ ግምታቸው 40 ሚሊየን ብር የሚጠጋ 20 ተሽከርካሪዎችን ተረከበ::

      ኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎቹ በከተማዋ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ለማደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ እገዛ አላቸው ብሏል፡፡ በርክክብ ስነስረአቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ ቡህና ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በስነስረአቱ ለይ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለረጅም አመታት በተሽከርካሪ እጥረት ሲቸገር መቆየቱን አስታውሰው አስተዳደሩም ይህን ከፍተት ለመሸፈን በተለያዩ ወቅቶች ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ በእለቱ ያደረግነው ድጋፍም የነበረውን ችግር ቀርፎ…

      Read More

        የመስቀል ደመራ በዓል ኮሮና ቫይረስን ታሳቢ ባደረገ መንገድ በድምቀት እንደሚከበር ተገለፀ::

        የመስቀል ደመራ በዓል ኮሮና ቫይረስን ታሳቢ ባደረገ መንገድ በድምቀት እንደሚከበር ተገለፀ ህዝበ ክርስቲያኑ በአሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማስታወስ ሊሆን ይገባል ተብሏል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪሃጅ ሊቀትጉሃን ማቲያስ በቀለ በሰጡት መግለጫ የደመራ በአል በተለመደው ሃይማኖታዊ ስርዓት እንደሚከበር ገልፀዋል። በዓሉ በርካታ ምዕመን አንደማሳተፉ ኮሮናን ታሳቢ ያደረገ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሊቀ ትጉሃን አሳስበዋል።አያይዘውም ይህ…

        Read More