ያሀገር ሽማግሌዎቹም ሆነ ኡጋዞቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃም በሁሉም መልኩ ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ ኡጋዞች ፤አባ ገዳ እና የሀገር ሽማግሌዎች በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ህወሀት በሰሜን እዝ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገታዊ ጥቃት በመፈፀም ባደረሰው ጥቃት ማዘናቸውንና ይህም የዚህ ቡድን የሀገር ክህደት ጫፍ መድረሱን አመላካች ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ ተሳታፊዎች እንደተገለፀው የሀገር መከላከያ አባላቱ በቅንጅት እየተወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃንም እንደሚደግፉ ጠቁመው እኛም የአካባቢያችንን ሰላም ነቅተን በመጠበቅ እንዲሁም ለሰላም ማስከበር ተልእኮ የተሰማራውን ሰራዊታችንን በሁሉም መልኩ ለመደገፍ ቃል እንገባለን ብለዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የድሬደዋ አስተደደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙሳ ጠሀና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የምስራቅ ኢትጵያ ፌደራል ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ኮማንደር ሰለሞን ከበደ እንደተናገሩት የሀገርን ሰላምና ፀጥታ የማከበር ተልእኮን ያነገበው ሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡም ነው ያሉ ሲሆን በዚህም ሁሉም የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
ለዚህም ኡጋዞች፤ አባ ገዳ እና የሀገር ሽማግሌዎችና ተሰሚነት ያላቸው አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘውገ አውላቸው
ለኦሮምኛ የድሬደዋ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዜናዎችን ለማግኘት ይሄን ሊንክ ይጠቀሙ


