የድሬዳዋ የዲያስፖራ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች በዘርፉ ያሉ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በአገራችን ዲያስፖራው ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆን የዲያስፖራ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ በመሆኑ አውንታዊና አበረታች ውጤቶች መመዝገቡን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ በወቅቱ ተናግረዋል። አክለውም በአስተዳደሩ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ጥያቄ በተገቢው መንገድ ለመፍታት በሚቻልበት መንገድ እተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።
በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት ጥያቄ ካቀረቡ 400 ከዲያስፖራዎች ውስጥ 200ዎቹ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ማውጣታቸውን 67ቱ በተለያዩ መስኮች ፕሮጀክት ቀርፀው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 23 ፕሮጀክቶች አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን 22 ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ እንሚገኙ 22 ፕሮጀክቶች ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ገጥሟቸው ያልጀመሩ መሆኑን ከንቲባው አብራርተዋል።
በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ የገቡ ፕሮጀክቶችም ለ1876 ሰዎች ቋሚና ኮንትራት ለ3ሺህ ሰዎች ጊዚያዊ የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን ከንቲባው አስረድተዋል።በዘርፉ ያሉ ችግሮች ከስር ከስር እተፈቱ ዲያስፖራውን ወደ አስተዳደሩ ለመሳብ የሚስችሉ ስራዎችን ለማከናወን ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተውጣጣ ስትሪንግ ኮሚቴ በማቋቋም እተሰራ መሆኑን ከንቲባ አቶ አህመድ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የድሬደዋ የዳስፓራ ጉዳዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር አቶ አክሊለ ታጠቅ በአስተዳደሩ ዲያስፖራው በቀጥታ በኢንቨስትመንት ተሰማርቶ የስራ እድል ከመፍጠር ብሎም ለኢኮኖሚው እድገት ትልቅ አቅም ከመሆን ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር ውስጥ ገቢ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል ።
ከዚህ አንፃር ከ2019-2012 ዓም ብቻ 120 ሚሊየን ዶለር ማለትም 3.5 ቢሊየን ብር በላይ ዲያስፖራው ለወዳጅ ዘመድና ቤተሰቦቻቸው በሬሚታንስ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ገቢ ሆኖል።በኮቪድ 19 በመከላከል ረገድ በውጭ አገራት የሚኖሩ የድሬደዋ ተወላጆች ያበረከቲት የተለያዩ ድጋፍ እንዲሁም ለችግረኛ ቤተሰብ ተማሪዎች እያደረጉት ያለው የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም እርዳታ የዲያስፖራውን የማህበራዊ ዘርፍ ተሳትፎ አመላካች እንደሆነ አቶ አክሊለ ጠቁመዋል ።
የድሬዳዋ የዲያስፖራ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች በዘርፉ ያሉ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ በተካሄደው በዚህ መድረክ በድሬደዋ ያሉ የዲያስፖራ አባለት የተሳተፉ ሲሆን በርካታ ሃሣብና ጥያቄዎች ተነስተዋል።
በቀጣይ በዘርፉ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው የድሬደዋ ብልግና ፓርቲ ፅ/ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ምንም እንኳን በሀገር ውስጥ በሚፈለገው መጠን ምቹ ሁኔታዎች ባይኖርም ዲያስፖራው እንቅፋቶችን ተቋቁሞ በአገር ፍቅር ስሜት በተለያዩ መስኮ ያለውን የገንዘብም ሆነ የእውቀት አቅሙን እንዲመነዝር አቶ መብራቴ ጥሪ አቅርበዋል።


