በወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው የተመራ የሚኒስቴሩ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ከተማ በመገኘት ከአመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች እና ከኢሳ ጎሳ መሪዎች ጋር ተወያዩ::
በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ከተማ ተገኝቶ የዞንና ወረዳ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች፣ የኢሳ ጎሳ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል:: የልዑካን ቡድኑ ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል በመገኘት በተመሳሳይ የማህበረሰብ እና አመራሮች ውይይት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ በውይይቶቹ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚበጁ ገንቢ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡…


