አምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች በቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በድሬዳዋ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ

    የአፋር ፣ የሱማሌ ፣ የኦሮሚያ ፣ የሃረሪ ክልሎችና የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃይሎች በአሁናዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ነው በድሬዳዋ ከተማ እየመከሩ የሚገኙት ።
    የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ ስብሰባውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፣ በቀጣናው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ፣ አልሸባብንና ሌሎች ፀረ ሰላም ሃይሎችን ከመቆጣጠር አንፃር ፣ ህገ ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሃይሉ ያለውን ዝግጁነት ይዳሰሳል ብለዋል ፡፡
    እንዲሁም አጠቃላይ ከአዳማ እስከ ጅግጅጋ – ጅቡቲ ያለውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ ያሉ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡
    በውይይቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያና የክልሎች ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
    (ምንጭ ፡- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት )