እንኳን ለ125ኛው ዓመት የአድዋ የድል በዓል በሰላም፣ በጤናና አደረሰን !

    የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ 125ኛ ዓመት የአድዋ ድል በዓል በእብሪትና በማን አለብኝነት ተነሳስቶ አገራችንን በቀኝ ግዛት ለመግዛት የሞከረውን የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር አባቶቻችን በአንድ ላይ በመሆን ድል በማድረግ ነፃነታችንን እንዳስከበሩት ሁሉ እኛም ዛሬ ዋነኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነት ላይ የተባበረ ክንዳችንን በማንሳት ብልፅግናን ልናረጋግጥ ይገባናል ብለዋል።
    በተለይም ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹን ታሪክና አኩሪ ገድል በሚገባ ተረድቶ እሱም በዘመኑ ለሀገሩ ሰላምን ከማስከበር አንስቶ የኛ የኢትዮጵያውያን እሴት የሆነውን ወንድማማችነትን በማጉላት የሀገራችን ህዝቦች አብሮ የመኖርና የመረዳዳት ባህል ወጣቱን በማስረዳት እንዲሁም ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ራሳቸውን እንዲያሸጋግሩ በመቅረፅ ትውልድን ማነፅና መልካም ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ከሁሉም አባቶችና ቤተሰብ ይጠበቃል።
    አድዋ የነፃነት ምሳሌ የአፍሪካውያን ክብር መሆኑን ገልጸው እንኳን በሰላም አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡