የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በስርአተ ምግብ ዙሪያ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

    በእቅድ ግምገማው በሴክተር ተቋማት የስርአተ ምግብ ተጠሪዋች በተቋማቸው የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።በቀረበው የእቅድ አፈፃፀም ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
    በእቅድ ግምገማው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ እንደተናገሩት ሴክተሮች ተቀናጅተው በመስራታቸው የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን በመግለፅ በእቅድ ተይዘው ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀጣይ ባሉ ጊዜያት በአጭር ጊዜ መከናወን አለባቸው ብለዋል ።