የጤናመድህን
ከጤናበላይምንአለ? ሰው ጤናውን ከሆነ ከራሱ አልፎ ለሌላው የሚተርፍሥራሊሠራይችላል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ለጤና ከሁሉ ነገር በፊት ቅድሚያ በመስጠት በተናጥልም ቢሆን በጋራ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ ድርቢያ ብር አንበሳያስር ነውና ብሂሉ ያለንን ዕውቀት፣ ጊዜ፣ አቅም እና ገንዘብ በማስተባበር ለጤናችን ዋስትና የሚሆንሥራ ልንሠራ ይገባል፡፡ ሰው ታክሞ ሊድን በሚችለው በሽታ መታከም ባለመቻሉ ሲሞት በለቅሶ ከመቅበር ክንዳችንን በማስተባበር ማሳከሙ ለሁላችንም እርካታ የሚሰጥነው፡፡ ስለዚህ በጋራ በመሆን በመረዳዳት እና በመደጋገፍ የጤና ዋስተናችንን አስተማማኝ ለማድረግ ባለን አቅም ሁሉር ብርብማድረግያስፈልገናል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋናው መፍትሄ በመሆኑ የሰለጠነው ዓለም በመተግበር ውጤታማ የሆነበትየጤናመድህንን በማደራጀት እና በማጠናከርመረባረቡነው፡፡ የጤናመድህን ማለት አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ ወይም ክፍያ ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የጤና መታወክ ባጋጠማቸው ጊዜ ካልታሰበ ከፍተኛ የህክምና ወጪ የሚጠበቁበት ስልትነው፡፡ይቀጥላል ….ለበለጠ መረጃ ገፅ 2 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 1
ከታላቁ የአድዋ ድል ምን እንማራለን?
በኋላ ቀር የውጊያ ሳይንስና በኋላቀር የጦር መሣሪያ እስካፍንጫው በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወቅቱ በጣም ከፍተኛ በሆ የውጊያ ሳይንስ የሚደገፈውን የጣሊያን እብሪተኛ ወራሪ ኃይልማሸነፍ ለሰማሁሉ ተዓምር ካልሆነ በቀር እንዴት ሊታመንይችላል ፡፡ ገድሉ እውነትና መተኪያ በሌላት ውድሀገራቸው ጉዳይ የማይደራደሩ ፤ ሀገራቸው ተደፍራና ተዋርዳ ከማየት የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አባቶቻችን የተፈጸመ ዘመን የማይሸረው ገድልነው ፡፡
የአድዋ ድል ዓለም በአንድ ጊዜ የተደመመበት ና ለአፍሪካ ብሎም በዓለም ላሉ ጥቁሮችና ነጻነት ውዳዶች ሁሉ ኩራት የሆነ ገድልነው ፡፡ በተለይ ወቅቱ ነጮች በጥቁሮች ላይ የነበራቸው የበላይነት ገኖ የነበረበት ወቅት ስለነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነጮች በአፍሪካ ምድር በጥቁሮች ለዚያውም ድሀና ኋላቀር በሚባሉት አባቶቻችን መፈጸሙ እብሪተኛ ነጮችን ሲያስደነግጥ ጥቁሮች ለነጻነታቸው እንዲቆሙ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረነው ፡፡ ለዚህም ነው የአፍሪካ የነጻነትና ሉዓላዊነት አርዓያ እንደሆንን አፍሪካውያንምአለምምበአንድድምጽያረጋገጠው ፡፡ይቀጥላል …ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 1
የሰው ወርቀ አያደምቅ
በእጃችን ያለውን ወረቅ
ዋጋውን እንወቅ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውግዘት እየደረሰበትያለውህገ – ወጥ የሰዎች ዝውውር በተደራጀና ጭካኔ በተሞላበት የማፍያሰነሰለት የሚመራ ወነጀል እንደሆነ በተከታታይየተደረጉ የውስጥና የውጭ ጥናቶች ያረጋግጣሉ ፡፡ በጥንት ዘመን የቀረውን አስከፊውን የባሪያ ንግድ ዓይነት በሰለጠ ነው በዚህ በ21ኛው ክ/ዘ ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ እተገበሩት መሆኑን በተለያዩ ጊዜዎች የሚሰሙ ሰቅጣጭ ዓለም አቀፍ ክስተቶችያመላክታሉ ፡፡ ህገ – ወጥየሰዎች ዝውውርን የሚመራው ኃይል በህገ – ወጥነትየተደራጀ ፣ ሚስጢራዊና መረቡ ከአውሮፓ ጀምሮ በእስያ፣ በላቲንአሜሪካ ፣ በአፍሪካና በዐረቡም ዓለም በስፋት የተዘረጋ የወንጀለኞች መዋቅርነው ፡፡ ይህ መዋቅር ከእርሱጋርየሚሠሩ በየአህጉሩና በየሀገሩህገ – ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚሠሩ ወኪሎች አሏቸው ፡፡ ከከተሞችና ከገጠር መንደሮች ወጣት ወንዶችንና ወጣት ሴቶችን ከወላጂቻቸው ፣ ከትዳራቸውና ከእረሻ ሥራቸው እያፈናቀሉ የተሸለ ሥራና ኑሮ ከፍተኛም ክፍያ ታገኛላችሁ ማማለያ ቃላት ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል አንዳንዴም ቤተሰብ ሳይሰማና ሳያውቅ በድብቅ እንዲኮበልሉያደርጓቸዋል ፡፡
ብዙዎች ከቀያቸውና ከሀገራቸው የሚወጡት የህንንህገ – ወጥየሰዎች ዝውውር የሚመሩትና የሚያደራጁት ህገ – ወጥ ደላሎች በሚያዘጋጁት መርሀግብርመሠረትነው፡የሀገራቸውን ጠረፍ ከተሞችና መውጪያ ኬላዎችን ይጠቀማሉ፡፡ እተባለው ሥፍራ ድረስ በተገኘው ትራንስፖረት ተጠቅመው ከደረሱ በኋላ በየቦታው በእነሱ መዋቅራዊ ሰንሰለት ውስጥ ያሉማረፊያ ቤትያላቸው ተቀባዮች አሏቸው፡፡ ደላሎቹ ለእነዚህ ሰዎችም ክፍያ ስለሚፈጽሙ ለጋራ ጥቅም የተደራጁ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ነው፡፡ በዚህ መልኩ መውጪያ ጠረፍላይ ከደረሱ በኋላ የጥበቃ ኬላዎችን በቀላሉ ለማለፍ ስለማይችሉ የተለያዩ ስልቶቻን ይጠቀማሉ ፡፡ ኬላዎቹን አሳብሮ በእግር በሌላ በኩል በማለፍ አካባቢውን በደንብ ጠንቅቀው በሚያቁ ሰዎች በመመራት ጥበቃ የሌለበትን ጫካ የጠረፍ አካባቢ በመምረጥ፤ወነዝ ካለም ዋናተኛ እንዲያሻግራቸው ተደርጎ ዕድላቸው ከቀናና በአውሬ ካልተበሉ ወደሌላ ሀገር መሬትይደርሳሉ፡፡ይቀጥላል …ለበለጠ መረጃ ገፅ 7ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 1


