ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2/2013 ዓ.ም የ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ሊሰጥ ነው፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በአስተዳደሩ ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈተና በኮቪድ-19 ምክንያት እንዲሁም በሀገር ደረጃ በኦንላይን(online) ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ለፈተና ሊውሉ የነበሩት ታብሌቶች ከውጪ አለመግባታቸውን ተከትሎ ነው እስከ አሁን ፈተናውን ለመስጠት ያልተቻለው ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ሙሉካ አክለውም በአስተዳደራችን የ2012 ዓ/ም…


