የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ ።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው የህግ ማስከበር ተልእኮ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በድሬዳዋ በሚገኘው የምስራቅ እዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው ይገኛል ። የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮም ማርች 8 የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በህክምና ላይ ለሚገኙ የሰራዊቱ አባላት የሚሆን የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን ድጋፍ አድርገዋል ። በድጋፍ ስነ-ስርአቱ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት…


