በአለም አቀፍ ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ ዘንድሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ባለዉ የአለም ሴቶች ቀን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ
“የሴቶች አመራር ሚና እና የኢትዮጲያ ብልፅግና ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደዉ ውይይት ላይ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሰሀለወርቅ ዘውዴ እንዳሉት የሴቶች ተሳትፎ እና ዕኩልነት ላይ አተኩረዉ ለሚሰሩ ጥናትና ምርምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስተር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ በበኩላቸዉ ማህበረሰቡ ሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሚነት ለማሳደግ የወጣቱ ሚና ከፊተኛ ነዉ ብለዋል ፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲው የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ደረጃ ላይ የደረሱ ሴቶችን ከማበረታታት አንፃር ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡


