በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች እራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ከመጠበቅ ባለፈ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታ በድሬዳዋ አስተዳደር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ፡፡ በሽታው በሀገራችን ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በድሬዳዋ አስተዳደር 32 ሺህ 209 ለሚሆኑ ሰዎች የናሙና ምርመራ በማድረግ 3 ሺህ 718 የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ድረስም ከበሽታው ጋር ተያይዞ በከተማዋ የ 45 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በሀገር አቀፍ ደረጃ…


