በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።
6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ ነፃና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆንና ምርጫውን በበላይነት በማሸነፍም የህዝብ ተወካዮች መቀመጫ የማግኘት ግቡን እውን ለማድረግ በሚያግዝ መልኩ ዛሬ ለፓርቲው የታችኛው መዋቅር አመራርና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው ። በስልጠናውም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸው አቋሞች ፣ ባለፉት 3 አመታት ፓርቲው ያሳካቸው ድሎችና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሰነቀው ህልም ለአባላቱ በሰፊው ተገልጿል…


