6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ ነፃና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆንና ምርጫውን በበላይነት በማሸነፍም የህዝብ ተወካዮች መቀመጫ የማግኘት ግቡን እውን ለማድረግ በሚያግዝ መልኩ ዛሬ ለፓርቲው የታችኛው መዋቅር አመራርና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው ።
በስልጠናውም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸው አቋሞች ፣ ባለፉት 3 አመታት ፓርቲው ያሳካቸው ድሎችና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሰነቀው ህልም ለአባላቱ በሰፊው ተገልጿል ።
ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ብልፅግና ፓርቲ የሚጠቀመው የምርጫ ስትራቴጂ ፣ ስነምግባር መመሪያ እንዲሁም የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ላይ አባላቱ የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከአመራሩ ጋር ውይይት ተደርጓል።


