የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን እና ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር 27,380,069.46 ብልጫ እንዳላው አስታወቀ::

    የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ ዛሬ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ወር እና የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከመንግስት ታክስ እና ከመዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር140,865,471.36 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 137,402,956.20 መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት የወሩን የእቅዱን 97.54በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ዕቅድ አፈፃፀም ከ2012…

    Read More