የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ ዛሬ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ወር እና የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከመንግስት ታክስ እና ከመዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር140,865,471.36 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 137,402,956.20 መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሰረት የወሩን የእቅዱን 97.54በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ዕቅድ አፈፃፀም ከ2012 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ24.89በመቶ ወይም በብር 27,380,069.46 ብልጫ እንዳለው በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ መንግስት በcovid-19 ወረርሽኝ ግብር ከፋዩ ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚ ጫና እንዲታደግ 120,000,000 ብር በላይ የደረገው ድጎማ ሳያካትት 1,267,936,139.77 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 1,075,575,415.17 መሰብሰቡን ገልፀዋል።
ይህም የዕቅዱን 84.83በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ይህ አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 12.18በመቶ ወይም በብር 116,766,722.85 ብልጫ እንዳለው ታውቋል፡፡
ይህ ስኬት የተገኘው የገቢ አሰባሰብ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች በአግባቡ ተግባራዊ በመደረጋቸውና ፣ በተለይም የህግ ተገዥነት ላይ ጠንካራ ስራ በመሰራቱ ፤ አስተዳደሩ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ የሰጠው ጠንካራ ትኩረት ፤ ታማኝና ከፍተኛ ግብር ከፋዬች ግብራቸውን በማሳወቅ በጊዜ መክፈል በመቻላቸው እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተቀናጅተው በመስራታቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡


