ከአፍጢር ፕሮግራሙ ጎን ለጎንም ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደርጓል ።
1442 ተኛውን ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በ 06 ቀበሌ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት የአፍጢርና ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የድጋፍ ፕሮግራም አካሂዷል ።
በስነ-ስርአቱ ላይም የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ሻኪር አህመድ በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጋራ በመሆን በማፍጠር አብሮነትንና ወንድማማችነትን ከማጠናከር በዘለለ ያለው የሌለውን በመርዳት አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል ።
የረመዳን ፆም በጋራ የሚፍጠርበትና አቅመ ደካሞች የሚረዱበት ወር እንደመሆኑ መጠን በተለይም ከተማችን ድሬዳዋ በመረዳዳትና በመደጋገፍ እንደመታወቋ መጠን ይሄንንም በረመዳን ፆም አቅመ ደካሞችን በመደገፍና አንድነታችንን በማጠናከር ማስቀጠል እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግረዋል ።
በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት ጎረቤትን ፣ ቤተሰብን እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን መርዳትና መጠየቅ የፅድቅ ተግባር እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም መሰል ተግባራቶች እንደሚቀጥሉም የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሁክሚያ መሀመድ ተናግረዋል ።
በአፍጢርና ድጋፍ በማድረጉ ስነ-ስርአት ላይም በ 06 ቀበሌ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም የአፍጢርና ድጋፍ የማድረጉ ተግባር ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይም ይሆናል ።


