የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ ጀመሩ::

    የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ መጀመራቸውን የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡
    ሁለቱ የውሃ ማስተንፈሻዎች ስራ የጀመሩት ግንባታቸው ተጠናቆና የሙከራ ስራ ተከናውኖባቸው መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ገልፀዋል፡፡
    ስራ የጀመሩት ማስተንፈሻዎቹ አጠቃላይ ዓመታዊውን የዓባይ ውሃ ፍሰት የማሳለፍ አቅም እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡
    ማስተንፈሻዎቹ በግድቡ ሙሌት ወቅት የዓባይ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ያለውን ፍሰት እንዲጨምር የሚያስችሉ ናቸውም ብለዋል ሚኒስትሩ።
    የውሃ ማስተንፈሻዎቹ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የሚኖረውን የውሃ ፍሰት እንደማያስተጓጎል ማረጋገጫ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
    ምንጭ:-EBC