በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤና ማበልፀግ ኬዝ ቲም የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር የምግብና ሥርዓተ-ምግብ የአፋፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡
በተዘጋጀው የአፋፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ መስሪያቤቶችና፣ ድጋፍ ሰጪዎች የአስተዳደሩ ብሔራዊ የሥርዓተ-ምግብ ተግባሪዎች የተገኙ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተግባሪ ተቋማት እንዲሁም በጤና ቢሮ ደረጃ በስርዓተ-ምግብ ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎችን የመገምገም፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎች የማስቀመጥ በቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራትና ለቀጣይ በጀት ዓመት ምን ይሰራ በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የምግብና ሥራዓተ ምግብ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ተጠሪ የሆኑት ሲ/ር ደመቀች መኮንን እንዳሉት በግምገማና ውይይት መድረኩ ላይ የአፈፃፀም ክፍተት የታየባቸው ፈፃሚ መስሪያ ቤቶች በቀጣይ አፈፃፀማቸውን እንዲያሻሽሉና በምግብና ስርዓተ-ምግብ አቅጣጫ የተቀመጡ ዕቅዶችን በመተግበር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የምግብ እጥረት ችግርን ለመፍታት ሃያ ፐርሰነቱ/ 20 % በጤናው ዘርፍ የሚፈታ ሲሆን ቀሪው እና ትልቁ ሰማኒያው ፐርተሰንት /80% ሌሎች መስሪያ ቤቶች የሚፈቱት ከመሆኑ አንፃር ሁሉም የሥርዓተ-ምግብ ተግባሪዎች ለሥርዓተ-ምግብ ትግበራው በጋራ በመስራት ችግሩን ሊፈቱ እንደሚገባ ሲ/ር ደመቀች መኮንን አሳስበዋል፡፡
የሥርዓተ-ምግብ ተግባሪዎች በተቋም ደረጃ ከሚበጅቱት በጀት ሁለት ፐርሰንት/ 2% ለሥርዓተ-ምግብ ትግበራ መመደባቸውና የአምስትና የአስር ዓመት የሥራ ዕቅዶቻቸው ውስጥ የሥርዓተ-ምግብ ተግባራትን ማካተታቸው እንዲሁም አስተዳደሩ ለትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ አምስት ሚሊየን ብር መመደቡ የሚያበረታታና አስተዳደሩ ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።


